Friday, May 1, 2015

በምእራብ እዝ የሚገኙ የአየር ሃይል አባላት ባልታወቀ ምክንያት ሞባይላቸውን እየተቀሙና እየተፈተሹ በካምፕ ውስጥ የቁም እስረኞች ሁነው እንደሚገኙ ተገለፀ።



    የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው ገዢው ስርአት በምእራብ እዝ የአየር ሃይል አባላት ላይ ከባድ ጥርጣሬ ስላለው የእዙ ሃላፊዎችን ሚያዚያ 16 2007ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰአት አስቸኳይ ስብሰባ ብለው በመስብሰብ ሞባይላቸውን በመቀማት እየፈተሹ ከካምፕ እንዳይወጡ እንደ ከለከሏቸው መረጃው ገልጿል።
   በተጨማሪም እነዚህ የኢህአዴግ አየር ሃይል አባላት በተደጋጋሚ ስርአቱን በመቃወም እየጠፉ ወደ ሚመቻቸው ቦታዎች በመሄድ ላይ እንዳሉና በርካታ ሞያተኞችም እንደታሰሩ የደረሰን መረጃ አስረድቷል።