Saturday, May 2, 2015

በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ የሚኖር ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ እየተከለከለ መሆኑና የተቃዋሚ ድርጅት አባላትም እየታሰሩ መሆናቸውን ተገለፀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል የደብረማርቆስ ከተማና አካባቢዋ የሚኖር ህዝብ በደቡብ አፍሪካ፤ በሊቢያና በየመን በንፁሃን ዜጎቻችን እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ ተግባር ለማውገዝ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድርግ ሲጠይቁ በኢ.ህ.አዴ.ግ ስርዓት የተከለከሉ ሲሆን ከ3 በላይ ለሚሆኑ የተቃዋሚ ድርጅት አባላትም ህዝብ ሊያነሳሱ ይችላሉ ከሚል ስጋት በመነጨ የሰሩት ወንጀል ሳይኖራቸው ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
    ከታሰሩ ወገኖች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል  አቶ ደጀን፤ አቶ እንዳለ ሽመልስና አቶ ሱልጣን በሽር የተባሉትና ሌሎችም የሚገኙባቸው በሌሊት ከመኖርያ ቤታቸው ታፍነው እንደተወሰዱ የገለፀው መረጃው በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ መከልከሉ ለዜጎቻችን ክብር አለመስጠት ነው በማለት በርካታ ወገኖች እየተቃወሙት መሆኑን የደረሰን መረጃ አስረድቷል።