Saturday, May 2, 2015

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት ባካሄዱት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት እየታሰሩ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አስረድቷል።



   በመረጃው መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  ተማሪዎች ሚያዝያ 16 ቀን 2007 ዓ/ም ባካሄዱት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት በስርዓቱ ካድሬዎች ለተከታታይ 3 ቀናት ግምገማ እንደተካሄደላቸውና የግምገማቸው አጀንዳም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ እነማን ናቸው? የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎችስ እነማን ነበሩ የሚል ርእስ ቢያቀርቡም ምንም ዓይነት ውጤት ሊያገኙ ባለመቻላቸው በጅምላ በርካታ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው እንዳባረሯቸው  ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
   መረጃው ጨምሮም በስልጣን ላይ ያለው ገዥው ስርዓት በተማሪዎች የተሰጠውን ሂስ ከማስተካከል ይልቅ ማንኛውም የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ,ን ስርዓት የተቃወመ ተማሪ ከትምህርት ገበታው ይባረራል እያሉ በማስፈራራት ላይ እንደሚገኙ  የተገኘው መረጃ አስታውቋል።