Saturday, May 23, 2015

በአማራ ክልል የሚገኙ የብአዴን ኢ.ህ.አ.ዴግ ካድሬዎች ህዝብ እንዲመርጣቸው ሲሉ ተቋማት እንሰራለን በማለት የመሰረት ድንጋይ እያስቀመጡ መሆናቸው ታወቀ።



  በአማራ ክልል የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች በመጪው ምርጫ ህዝብ አይመርጠንም የሚል ከባድ ስጋት ስላደረባቸው የህዝቡን ትኩረት ለመሳብ ከግንቦት 10 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምረው የተለያዩ ተቋማት እንገነባለን በማለት የመሰረት ድንጋይ እያስቀመጡ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ህዝቡ ግን የማታለል ተግባራቸውን ስለተረዳው “እስካሁን የት ቆይታችሁ ነው ምርጫ ሲመጣ ለማስመሰል የመሰረት ድንጋይ የምታስቀምጡት ምርጫ እስኪያልፍ ህዝቡን ለማደናገርና ለማታለል እንጂ ለመጥቀም አስባችሁ አይደለም በማለት እንደተቃወማቸው ታውቋል።
  ይህ በስርዓቱ እየተፈፀመ ያለው የማታለል ተግባር በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚታይ የማደናገር ስልት መሆኑን የክልሉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።