Tuesday, May 26, 2015

በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴና ኣርጃ ከተሞች የሚኖረውን ህዝብ የኦህዴድ/ኢህአዴግ ካድሬዎች ወደ ሰልፍ ውጣ እያሉ እለታዊ ኖሮውን እንዳያሳልጥ እያሰናከሉት እንዳሉ ታወቀ።



   በነቀምቴና አርጆ ከተሞች የሚገኙ የኦህዴድ/ኢህአዴግ ካድሬዎች ነዋሪው ህዝብ ስርአቱ ወደ ጠራው ስብሰባ  ሰለማዊ ሰልፍ በማድረግ ድጋፉን እንዲገልፅ ግንቦት 12/2007 ዓ/ም ለተደረገለት ጥሪ ህዝቡ አንወጣም በማለቱ ምክንያት በከተሞቹ የሚገኙ ስራ አጥ ወጣቶች ከ300 ብር በላይ በመክፈል ኢህአዴግን ምረጡ፤ ህዝቡ ኢህአዴግን መምርጥ እንዳለበት ቀስቅሱት እያሉ በተጠቀሰው እለት በማታለል ተግባር ላይ እንደተሰማሩ ለማወቅ ተችሏል።
     የኢህአዴግ ስርአት ስልጣን ላይ የሚያስቀጥለውን ድምፅ ለማግኘት ሲል በተለያየ ጥቅማ ጥቅምና በገንዘብ በማታለል ተግባር ላይ ተስማርቶ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው እነዚህ በስርአቱ 300 ብር የተከፈላቸው ሰዎች ግን በገንዘብ ተታልለን ህዝብ ለዚህ አደናጋሪ ለሆነው ስርአት ምረጡት እያልን አንቀሰቅስም፤ ለራሳችንም አንመርጥም ሲሉ እንደተቃወሙት ለማወቅ ተችሏል።