Tuesday, May 26, 2015

በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶችን ወደ ውትድርና እንዲገቡ በህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት የተካሄደው ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ እያጋጠመው መሆኑን ተገለፀ።



      ከፍተኛ የህወሓት/ኢህአዴግ ካድሬዎች በተለያዩ የትግራይ ክልል ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ህዝብ ስብስበው ወጣቶችን ወደ ውትድርና መግባት እንዳለባቸው በሚል ቅስቀሳ በማካሄድ ተጠምደው ባሉበት በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ እየተቃወማቸው እንዳለ የገለፀው መረጃው በተለይ በአሕፈሮም ወረዳ ወርዒ-ለኸ የሚኖር ህዝብ ልጆቻችንን የጥቂት ባለስልጣናት ጥቅም ለማስከበር ብለን ባልተፈለገ ቦታና ጊዜ ህይወታቸውን እንዲገብሩ ወደ ውትድርና አንልክም እንዳሏቸው ምንጮቻችን ገልፀዋል።
   ተቃውሞውን የታዘቡት የህወሓት መሪዎች መፍትሄ ለማፈላለግ በሚል ዝግ ስብሰባ ባካሄዱበት ሳምንት” የትግራይ ህዝብ ስለምንድነው ከኛ እየራቀ ያለው የሚል አጀንዳ በማንሳት የተነጋገሩ ቢሆኑም ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ሳያስቀምጡ ከስብሰባው እንደተበተኑ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን አስታውቋል።