Thursday, July 30, 2015

በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ሃውዜን ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ኢንቨስት ለማድረግ ከውጭ ለመጡት ዜጎቻችን ከህዝብ ጋር እያጣሏዋቸው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



     የሃውዜን ከተማ አስተዳዳሪዎች ከውጭ መጥተው በትውልድ ሃገራቸው ድርጅት ከፍተው ለማልማት የሚንቀሳቀሱትን ኢንቨስተሮች እያንገላትዋቸው እንደሆኑ የገለፀው መረጃው ከኢንቨስተሮቹ አንዱ አቶ ፍፁም ገብረእግዛብሄር የተባለው ከአሜሪካ መጥቶ በሃውዜን ከተማ ሆቴል ገንብቶ ለመስራት ሲጀምር የወረዳው ዋና አሰተዳደሪ የሆነው አሕፈሮም ወልደገብሪኤል የተባለው ባለ ስልጣን በስብሰባ ላይ ሂስ ስላደረገው ህዝቡን ሰብስቦ “ ይህ ሰው የዓረና ተላላኪ በመሆኑና ፀረ ልማታዊ መንግስታችን እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ ወደ ሆቴሉ ሰው ገብቶ እንዳይዝናና “ በማለት ፀረ ልማት የሆነው ትእዛዝ እንዳወረደ ለማወቅ ተችሏል።
    በአስተዳዳሪው ትእዛዝ ስጋት ላይ የወደቀው ህዝብም ወደ ሆቴሉ መግባት በማቋረጡ ምክንያት የድርጅቱን ባለቤት ለከባድ ኪሳራ እንደተዳረገ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።