Thursday, July 30, 2015

የመቐለ ከተማ ነዋሪ ህዝብ አግባብነት በሌለው የግብር አከፋፈል ተማርሮ ሰለማዊ ሰልፍ ልንወጣ ነው በማለቱ የተነሳ ቅሬታችሁን በፅሁፍ አቅርቡ ሲሉ የስርአቱ ካድሬዎች እንዳስገደድዋቸው ታወቀ።



     ምንጮቻችን ከከተማዋ እንደገለፁት የመቐለ ከተማ ነዋሪ ህዝብ አግባብነት በሌለው የግብር አከፋፈል በመቃወም የሃገር ሽማግሌዎች ወደ መቐለ ከተማ ፅህፈት ቤት በመሄድ ግብር ከአቅማችን በላይ ሁኖብናል፤ የተወሰነብንን ግብር ለመክፈል ደግሞ አቅም እንደሌለን ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ ፍቃድ ይሰጠን በማለት በጠየቁበት ጊዜ የስርአቱ ባለስልጣናት ደግሞ ቅሬታችውን በፅሁፍ እስከ ሃምሌ 30 /2007ዓ/ም ማስገባት እንዳለባቸውና ከዚህ ወጥተው  ሰልፍ ካደርጉ ግን ፀረ ሰላም ሃይሎች በመካከላቸው ለመግባት ሁኔታዎች የሚፈጥር ነው በማለት። የማስፈራሪያ መልስ ስጥተው እንደሸኙዋቸው ለማወቅ ተችሏል።
      መረጃው ጨምሮ በአሁኑ ጊዜ እየታየ ያለው የግብር አከፋፈል አንድ ነጋዴ 100ሺ ብር እንዲከፍል ከተተመነበት ቅሬታ አለኝ ብሎ የሚያመለክተው ግማሹን ከፍሎ ቅሬታውን ለማቅረብ እንደሚችል አዋጅ እንዳወጡና በተለይም በሓድነት ወረዳ የግብር ሰብሳቢ የሆነው መሰለ የተባለ ግለሰብ ከአራት የስራ ባልደረቦቹ በመሆን አግባብነት በሌለው አስራር ለነጋዴዎች ከልክ በላይ ግብር እየገመተ እንዳለና እሱን የሚያውቁት ግን ዝቅተኛ ግብር እንዲከፍሉ እየተመነላቸው መሆኑን መረጃው ይስረዳል።