Tuesday, September 29, 2015

በማእከላዊ ዞን ኣሕፈሮም ወረዳ የሚገኙ ኣርሶ ኣደሮች ቅድመ ዝግጅት ሳያድርጉና ካሳ ሳይሰጣቸው የእርሻ መሬታቸውን መነጠቃቸውና የሚኖርበት ቤታቸውም ስለፈረሰባቸው ለችግር መዳረጋቸው ታወቀ፣



እነዚህ በኣሕፈሮም ወረዳ ክሳድ ዕረ በሚባለው ቀበሌ የሚገኙ  ከ40 በላይ የሚሆኑ ኣርሶ ኣደሮች  ተግቢው ካሳ ሳይሰጣቸውና   ለቅድመ ሁኔታ ግዜ ሳያመቻቹ ለኣስፋልት መንገድ  መስሪያ  በሚል ሰበብ ለዓመታት ያለሙትን የእርሻ መሬታቸው ተነጥቀውና መኖሪያ ቤታቸው ስለፈረሰባቸው ከነቤተሰቦቻቸው ለከባድ ችግር  መጋለጣቸውን የገለጸው መረጃው እነዚህ የተበደሉ ዜጎች መፍትሔ ለማግኘት ለሚመለከታቸው  የመንግስት ባለስልጣኖች ያቀረቡት ኣቤቱታም ምንም ኣወንታዊ ምላሽ ስላላገኘ በስርኣቱ ያላቸወን ጥላቻ በምግለጽ ላይ መሆናቸው ታወቀ፣
  መረጃው ጨምሮም  ለመሬትም ይሁን ለመኖሪያ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ዜጎች ካሳ መክፈያ  ተብሎ ከፌደራል  በጀት ቢወጣም እነዚህ ከወረዳ እስከ ክልል ያሉት ባለስልጣናት  ለግል  ድርጅቶቻቸው መስሪያ እያዋሉት  ስለሆኑ  በደላቸውን ሰምቶ ፍትሕ  የሚሰጣቸው ኣካል እንደሌለ ገልፃዋል፣