Tuesday, September 29, 2015

በሳሓርቲ ሳምረ ወረዳ የሚገኙ ወጣቶች በማሕበር ተደራጅተው በሕጋዊ መንገድ የተሰጣቸውን መሬት የወረዳው ኣስተዳዳሪዎች በመቅማት ጉቦ ለከፈሏቸ የግል ባለሃብቶች እንደሰጡት በአከባቢው የሚገኙ መረጃዎች አመለከቱ፣



በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን  ሰሃርቲ  ሳምረ ወረዳ  ሓድነት ቀበሌ  የሚገኙ ወጣቶች በሕጋዊ መንገድ በታደላቸው መሬት ላይ ቤቶችን ሰርተው ንቦችን በማራባትና የተለያዩ  ተክሎችን  በማልማት ሲጠቀሙበት የቆዩትን መሬት   የወረዳው አስተዳዳሪዎች በመቀማት  ጉቦ ለሰጧቸው  የግል ባለሃብቶች እንዳደሉት ተገለፀ፣
      እነዚህ በማሕበር ተደራጅተው ሲሰሩ የቆዩት ወጣቶች ለምንድነው ወገናዊነት የሚፈጸመው  በማለት ለሚመለከታቸው ኣካሎች ኣቤቱታቸውን ቢያቀርቡም “ እኛ  ሰለዚህ ጉዳይ የምናውቀው የለም የሚል የሸፍጥ ምላሽ የመለሱላቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው፣ በዚህ ሳቢያም  ወጣቶቹ ከእጅ ወድ ኣፍ  የሚሆን ምግብ ሰላጡ ተበታትነው እግራቸው ወዳኣመራው ወደ ከተሞችና ወደ ጎረቤቶት ሃገሮች እየተሰደዱ መሆናቸወን አክሎ አስረድቷል