Wednesday, September 9, 2015

የህዝቦች ጥያቄ በየውለታ ቃላት አይፈታም፥



   የኢትዮጵያ ህዝብ ከነበረው ፋሽስታዊ  ወታደራዊ የደርግ ስርዓት ለመላቀቅ የሰው ህይወትና ንብረትን የጠየቀ መራራ  ትግል አካሂዶ  ደርግን አሽንፏል።
   ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ፀረ ደርግ ኢሰፓን  ታግሎ በከፈለው መሰዋትነት የተመኘውና የታገለለት አላማ ሙሉ በሙሉ ግቡን ሊመታ  አልቻለም ብቻ ሳይሆን በህወሃት ኢህአዴግ ተክዷል።
ኢህ.አ.ዴ.ግም ሆነ ከስሩ የሚገኙ ድርጅቶች በተለይም ህወሓት  የ12ኛውን  ጉባኤው ለማሳለጥ የመቐለ ጎዳናዎች በሁሉም  አቅጣጫ የመቐለ ከተማ ኗሪ ህዝብ  እንቅስቃሴ በመሰጋት  እስከ ኢህ.አ.ዴ.ግ ጉባኤ የመጨረሻ ቀን  መፈናፈኛ በማሳጣት ህዝብ  ከቦታ ቦታ ተዝናንቶ  እንዳይንቀሳቀስ  አድርገውት  እንደከረሙ  ብዙ ምርምር የሚያስፈልገው አይደለም።
ተካሂዳል እየተባለ ያለው የህወሃት የኢህ.አ.ዴ.ግ የደ.ኢ.ህ.ዴን የብ.አ.ዴ.ን የኢህ.አ.ዴ.ግን የስልጣን ዕድሜ  ለማራዘምና እሱን የሚመሩ ባለ ስልጣናት  ካድሬዎች የስልጣን ዘመናቸውን በማራዘም የህዝብና የሀገርን ሀብት  በመቦርቦር ሚሊየነሮች ለመሆን ካልሆነ በስተቀር ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ  የሚያስገኘው ፋይዳ  ቅንጣትም እንደሌለ መታወቅ አለበት።
ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ በአሁኑ ሰዓት በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ መሬት ላይ ውድቆ ባለበት ጊዜ  በጉባኤያችንም በርካታ   የህብርተሰብ ከፍል የተገኘበት ጉባኤ ነው ብለው መናግራቸው በህዝብ ላይ ያላቸውን  ንቀትና አመለካከት  የሚያንጸባርቅና ህዝብን ያህል  የማያከብሩ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው።  በጉባኤያቸው ላይ አጋር ድርጅቶች እያሉ የሚጠሯቸው  የህዝባቸውን ችግርና ዴሞክራሲያዊ መብቱን የማያከብሩና  በህግ የበላይነት ላይ የማያምኑ ካድሬዎች  ስለተገኙ የህዝብ ወኪሎች  ተገኙ ብሎ መናገራቸው የሚገረም ነው።
   የኢትዮጵያ ህዝብ  ከ1950ዎች  አጋማሽ ጀምሮ የዲሞክራሲ፤ የሰብዓዊ መብት፤  የህግ የበላይነት ይከበርና የኢትዮጵያ ህዝብ የሀገሩ ሃብት ተጠቃሚ  ይሁን ሀገር የጥቂቶች ብቻ ሳትሆን የመላው በሉዓላዊ ግዛቷ የሚገኝ ዜጋ ነች የሚሉና በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች መሰዋእት በማድረግ አምባገነን ገዥዎችን በተባበረው ክንዱ ከመንበረ-ስልጣናቸው ቢያስውግዳቸውም ዛሬም በድጋሜ በህዝብ ልጆች መሰዋዕትነት ስልጣን የተቆናጠጠው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ገዥዉ ቡድን የህዝብን ጥያቄዎች በማፈን የስልጣን ዘመኑን ለማራዘ ላይ ታች በማለት ላይ ይገኛል።
ይሁን እንጂ ለ24 አመት  ሙሉ  የኢትዮጵያ ህዝብ ነገ ይሻል ይሆናል ይለወጣል በማለት   በትግስት ለተወሰኑ አመታት ሲጠብቅ ከቆየ በኋላ ለውጥና መሻሻል ስላላገኘና በተለያዩ መንገዶች ፀረ ኢህአዴግ ትግሉን በማቀጣጠል  በአሁን ሰዓት ለስርዓቱና ለአመራሮች  የእግር እሳት ሆኖ እያቃጠቸው  ሲሆን የህዝብን አንገብጋቢ ጥያቂዎች ማለትም የማህበራዊ፤ የፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ዛሬም ልክ እንዳለፉት ጉባኤዎች ቃል ከመግባትና አቋም ከማውጣት በዘለለ ምንም ለውጥ ማምጣት  እንደማይችሉ የሚያጠራጥር አደለም።
የህወሃት 12ኛ ጉባኤ ይሁን ሶስቱም የኢ,ህ,አ.ዴ.ግ አባል ድርጅቶች ክራይ ሰብሳቢነት በባሰ መልኩ እንዲቀጥል በማድርግ በአገራችን የብዙሃን ፓርቲ ስርአት እንዳይኖር 1ለ5 በሚል አደረጃጀት   ህዝቡን አፈነው በመያዝ  በሌላ መልክ ደግሞ ጥቅማጥቅምና የመንግሰት ሰራ እንዳይዝ በማደረግ ፍትሃዊና ደሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ባልተካሄደበት ምርጫ በጠመንጃ ህዝብ እንዲሸማቀቅ በማድረግና  አጭበርብሮ ባገኘው ድምፅ  ሙሉ በሙሉ አሸነፍኩ በማለት  ለአለም  ህብረተስብ የመነጋገሪ  እርእስ የሆነውን  አካሂዳቸው ህጋዊነት ለማልበስ  ባለፍት ሳምንታት በአካሄዱት  ጉባኤቸው ላይ የብዙሃን ፓርቲ   ስርዓት   አውራ  ፓርት ሆኖ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተመረጠ ቢሉም በህዝብ በኩል የቀረበላቸው  የለውጥ  የተለያዩ ጥያቄዎች  ያልመለሱና መመለስ የማይችሉ ፓርቲና መንግስት ህዝባዊ አደራ ተግባራዊ ሊያደረግ ፈጽሞ አይችልም።
ሁሉም በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አባል ድርጅቶች የሚገኙ መሪዎች በተለይ ደግሞ ህወሃት ጠለቅ ያለ በአመራሩ  ላይ ፍተሻ እንዲያደርግ  በቂ ግዜ ስጥቶ   ሂስና ግለሂስ እንዲደረግ ጥሩ መማማር ያለው ገንቢ  በትግል ላይ የተመሰረተ  አንድነቱን የሚያጠናክር ስራ እንደሰራ በየግዚያዊው የህወሃት ኣፈ-ጉባኤ በደብረፅዮን በኩል ሲናገር ተሰምቷል።
 ሆኖም ግን የነበረው ሂስና ግለሂስ የአመራር ጥንካሬውንና  ድክመቱን እንዳያይና ለህዝብና ለሀገር የሚጠቅም ውሳኔ ለማሳለፍ ሳይሆን በህወሃት አመራር መሃል ተፈጥሮ ያለውን መሰነጣጠቅ፤ በጥላቻ አይን መተያየትና ከሁሉም የባሰ ደግሞ በሙስና የጨቀዩ እርስ በራሳቸው በስጋት ውስጥ  ስላሉ ”ሾላ በድፍኑ” እንዲሚባለው ሆኖ ውስጣቸው በቅንነት መፈተሸ አልቻሉም። 
ይህ ሆኖ ሳለ ግን በአመራሩ መካከል አመታት ያስቆጠረ ያለመተማመን የፈጠረው ስጋት ስላለ እነማንን እናስውግድ?  እንማን ናቸው? ስልጣናችንና ጥቅማችንን የሚፃርሩ ላሏቸው ዜጎች ማጥፊያም ማስመሰያ በመፍጠር ህጋዊነት አላብሰው ለትግራይ ህዝብ በአጠቃላይ  ለኢትዮጵያ ህዝብ በጥሩ ሁኔታ  እንዳሉ አስመስለው ትልቅ የማሰናበቻ ወረቀት  በፍሬም አድርገው በመስጠት  መተካካት የሚል ስም በመሰጠት ያካሂዱት ማባረር ሂደት  መሆኑን ህዝብ መረዳት አለበት።
ስለዚህ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ለማስመሰል ኪራይ ሰብሳቢነትን በማሸነፍ የልማት ጎዳና ይዤ እየተጋዝኩ ነው ቢልም ፈፅሞ አንድም ሁለቴ ህዝብን ማታለል ይችላል፣ አታለዋልም፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ፈፅሞ ህዝብን ማታለል እንድማይችሉ አንዳንድ ለህዝብ የሚቆረቆሩ ሀቀኛ የህዝብ ልጆች  በህወሃት ኢ.ህ.ዴ.ግ ውስጥ ያለውን ጉድ ጎርጉረው  በማውጣት አጋልጠዋል፣ ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ላነሳቸው ህዝባዊ ጥያቄዎች በየውለታ ቃላት ብቻ አይፈቱም፣ እናም የኢትዮጵያ ህዝብ ፀረ-ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ትግሉን ማነሳሳትና ማቀጣጠል አለበት።