Tuesday, September 29, 2015

በትግራይ ክልል በማዕከላዊ ዞን የሚገኙ የድርጂት ባለቤቶች በኤሌክትሪክ እጥረት ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ መስራት እንዳልቻሉ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ፣



ከስፍራው የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በቆላ ተምቤን ወረዳ የሚገኙ የግል ድርጅት ባለቤቶች ህዝባቸውን የሚያገለግሉበት የነበረው በኤሌክትሪክ የሚሰራ የግል ድርጅታቸው በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ማምረት የሚችለውን ያህል ሊያመርት እንዳልቻለና ለኪሳራ እየተዳረጉ  መሆናቸውን አስረድቷል፣
መረጃው ጨምሮም ይህ የመብራት መቆራረጥ ችግር በህዝባዊና በመንግስታዊ ድርጅቶች እያወረደው ያለው ችግር ቀላል አለመሆኑን ከገለፀ በኋላ ይህ የመብራት መቆራረጥ  ችግር በቆላ ተምቤን ቻ ሳይሆን በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ እየታየ ያለ ችግር መሆኑን ከዚህ በፊት በዜና እወጃወቻችን መግለፃችን ይታወሳል፣