Tuesday, September 29, 2015

በሃውዜን ወረዳ ስሉህ ቀበሌ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች የመኖሪያ ቤት መስሪያ መሬት በማደል በኩል አድሎ እየፈፀሙ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ፣



በመረጃው መሰረት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ሃውዜን ወረዳ ስሉህ ቀበሌ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች የመኖሪያ ቤት መስሪያ መሬት እደላን በተመለከተ በጥቅምና በጉቦ ለሚቀርቧቸው ቤተሰቦቻቸው እያደሏቸው መሆናቸውን የገለፀው መረጃው። በርካታ ወጣቶች ከ3 ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ሲያቀርቡት የቆዩት አቤቱታ ሰሚ በማጣቱ ከቤተሰቦቻቸው ተደርበው እንዲኖሩ መገደዳቸውንም መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣
በመረጃው መሰረት በሃገራቸው ሰርተው ኑሮአቸውን እንዳይመሩ በመልካም አስተዳደር እጥረት ምክንያት ወደ ከተሞችና ሃገራቸውን እየጣሉ ወደ ስደት እንደሚሰደዱ የገለፀው መረጃው በዚህ ምክንያትም የሞት አደጋ ተጋላጮች እየሆኑ እንዳሉ የደረሰን መረጃ ገልጿል፣