Wednesday, September 9, 2015

በመቐለ ከተማ እየተካሄደ በነበረው የኢህኣዴግ ጉባኤ የትህዴን በራሪ ወረቀት በመበተኑ ከተማዋ በታጣቂ ተከባ መሰንበትዋን ለማዋቅ ተችሏል።



    በነሃሴ መጨረሻ ወር ኣከባቢ እየተካሄደ በነበረው የኢህኣዴግ ጉባኤ የተገኙት የስርኣቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ሌሎች የጉባኤው ተሳታፊ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ በራሪ ወረቀት በተለያዩ የመቐለ ከተማ ጎደናዎች የተሰራጨ መሆኑን ማወቃቸው ተከትሎ ክፉኛ መደንገጣቸውና፣ ጉባኤው እስከ ሚጠናቀቅ ደግሞ የፌዴራልና የክልል ፖሊሶች ተሰማርተው ከተማዋና ጉባኤተኞቹ ለመጠበቅ በሚል ተከባ መቆየትዋ ታውቀዋ`ል።
    በራሪ ወረቀቶቹ በተሳካ ሁኔታ እንደተዘረጋና ህዝብ ኣስፈላጊ የሆነ የትግል እንቅስቃሴ እንድያረግና ትህዴንን በተመለከተ ተጨማሪ በቂ መረጃ እንድያገኝ ያስቻለ ሲሆን የኢህኣዴግ ባለ ስልጣናት በከባድ ጭንቀትና ሽበራ በመውደቃቸው የሞት ሽረት እርምጃ እንዲወስዱ ያስገደደ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስታውቀዋል።