Thursday, October 15, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ተመድበው ሲሰሩ ከቆዩት ከ800 በላይ ሰራተኞች በመቀነሳቸው ምክንያ ለከባድ ማህበራዊ ችግር እንደተጋለጡ ታወቀ።



      በመረጃው መሰረት የኢህአዴግ ካድሬዎች ስልጣናቸውን ለማደላደል ሲሉ ላይና ታች በሚሉበት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር ባሉት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ሲሰሩ የቆዩትን ሲቪል ሰራተኞች 800 የሚሆኑትን በተለያዩ ምክንያቶችን በመፈጠር በዚህ ሳምንት ውስጥ ተቀንሰው እንዲወጡ በመደረጉ ምክንያት ያለ ስራ ተጥለው በመቅረታቸው የተነሳ ቤተሰቦቻቸው ለከባድ ማህበራዊ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ተገለፀ።
     መረጃው በመጨመር ከሲቪል ሰራተኞች ጋር የትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛ ነው ተብለው ከሃላፊነታቸው የተቀነሱት የገዢው ቡዱን ካድሬዎች ግን በመንግስት ልዩ ትኩረትና ድጋፍ ተደርጎላቸው በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅተው እንዲሰሩና ከሌላው ዜጋ የበለጠ ሃብት አፍረተው እንዲኖሩ ሁኔታዎችን እንደተመቻቸላቸው ምንጮቻችን በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
አስተዳደሩ በሙስና የተጨማለቁ ከፍተኛ አመራሮችና ሲቪል ሰራተኞችን ህግ ፊት በማቅረብ እንዲ ጠየቁ እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ቢገልፅም በተግባር ግን የበታች ሲቪል ሰራተኞች ለመክሰስ መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ ሲሆን ይህ ግን ወደ በላይ አመራሮች እንዳይሸጋገር ታስቦ እየተከተለው ያለው የስርአቱ አስመሳይ አካሄድ እንደሆነና ከዚህም አልፎ እርምጃ እንዲወስድ የፖለቲካ ቁርጠኝነቱን እንደሚያንሰው የህግ ባለሞያዎች ዋቢ በማድረግ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።