Thursday, October 15, 2015

ከአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ መምህራን በገዢው ኢህአዴግ ስርአት የተዘጋጀው የፖለቲካ ስልጠና ለመሳተፍ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ለቀሩት ደሞዛቸው እንዳይወስዱ መታገዳቸው ተገለፀ።



    በአዲሱ አመት 2008 ዓ/ም በገዢው ኢህአዴግ ስርአት የተዘጋጀው የፖለቲካ ስልጠና ለመሳተፍ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ለቀሩት የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ መምህራን ደሞዛቸው እንዳይከፈላቸው በመታገዳቸው ምክንያት የሚበሉትና የተከራዩትን የቤት ክራይ መክፈል አጥተው እጅግ እንደተቸገሩ ተጎጅዎች ዋቢ በማድረግ የተገኘው መረጃ አስረድቷል።
    በስብሰባው የተገኙት የገዢው ስርአት አጫፋሪዎች የሆኑት አንዳንድ መምህራን ደሞዛቸው እየተከፈላቸው በተጨማሪ ደግሞ ከመንግስት በጀት ከልክ በላይ ኣበል ሲታሰብላቸው፤ የስራ እድገትና የቦታ ዝውውርም እንደፈለጉት እንደሚከናወንላቸው የገለፀው መረጃው በስልጠናው ያልተሳተፉት መምህራን ግን በስርአቱ ካድሬዎች እንደ ጠላት ተቆጥረው ምክንያቶችን በመፍጠር ደሞዛቸው በመከልከል ሞራላቸው እንዲነካ በማድረግ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ መረጃው አስታውቋል።
በተመሳሳይም። የሃዋሳ ዩንቨርስቲ መምህራን በኢህአዴግ ስርአት የተዘጋጀውን የፖለቲካ ስልጠና እንዲሳተፉ ለማድረግ ታስቦ። ከከተማዋ ውጭ እንዳይንቀሳቀሱ ስለታገዱ። በስብሰባው ለመሳተፍ ፍቃደኛ ያልሆኑት መምህራን  ምሬታቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣