Friday, October 30, 2015

በስነ ምግባር ያልታነፁ የገዢው ኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አባላት ያለ ፍቃድ ከተማ ሄዳቿኃል እየተባሉ አብዛኛዎቹ ወታደሮች ቅጣት እየተቀጡ እንደሚገኙ ተገለፀ።



ምንጮቻችን የላኩት መረጃ እንደሚያመለክተው በሰሜን እዝ ውስጥ  በሚገኙ የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት ክፍለ ጦሮች በፈለጉት ጊዜ ወደ ከተማ እንዲሄዱ ስለ ማይፈቀድላቸው በዚህም የተነሳ በራሳቸው ፍቃድ ጠፍተው ወደ ከተማ በሚሄዱበት ጊዜ ደግሞ ሃላፊዎቻቸው ለምን ከተማ ሄዳችሁ በሚል ወታደራዊ ቅጣት የሚቀጡ ወታደሮች በርከት ያሉ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
        መረጃው ጨምሮ የስርአቱ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከመጀመሪያውም ውትድርናው አምነው የተሰለፉ ሳይሆኑና በድስፕሊን የታነፁ ስላልሆኑ። በጥርነፋ አይን እንዲያከብሩ የወረደላቸው መምሪያ ፍፁም በቁም ነገር ስለማይቀበሉት ደስ ባሰኛቸው ጊዜ የሚያቀርቡት ጥያቄ ሳይመለስላቸው ሲቀር እንደ መፍትሄ የሚወስዱት ራሳቸው ጥርነፈ ስተው ወደ ከተማ መግባት እንደ መፍትሄ ስለ ሚጠቀሙለት ወታደሮቹ ለኣንድ ጥፋት የተለያየ ቅጣት እየተቀጡ ማየት የተለመደ እንደሆነና ከዛም ባለፈ ያለ ፍቃድ ወደየ ክልሉና ወደ ከተማ የሚሄድ ወታደር በተደጋጋሚ የሚያጠፋ  በሚል ታስሮ የሚሰቃይ ቡዙ እንደሆነ መረጃው አስገንዝቧል።
በሚሰጣቸው የቅጣት  ክብደት አይነት ለአንዱ ቀላል ያለ ለሌላውም ከባድ በመሆኑ የተነሳ ወታደሮቹ ባገኙት አጋጣሚ ጠብቀው መሪዎቻቸው በመግደልና ውትድርናውንም ጥለው እንደሚጠፉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።