Saturday, October 24, 2015

ሃገር ተረካቢ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ወደ ስደት በማቅናት በረሃንና ባህርን አቆረጠው ሲጎዙ አሳዛኝ ወደ ሆነ አደጋ እየተጋለጡ መሆናቸው ተገለፀ።



         በስራ ማጣት ምክንያት ማህበራዊ ኑሮአቸውን ሊመሩ ስላልቻሉ 317 ኢትዮጵያውያን  ወጣቶች ወደ ደቡብ አፋሪካ  ለሰደት በሚሄዱበት ጊዜ በማሊ ፖሊሶች  ተይዘው እሰር ቤት ተዘግተው እንዳሉ የገለጠዉ መረጃዉ የአገሩ ፍርድ ቤት የወሰነላቸው የገንዘብ የእስራትና ቅጣት ቢጨርሱም የሚከታተልላቸው የህግ ጠበቃ የሚሆንላቸዉ አካል ባለማግኘታቸው የተነሳ እስከ አሁን ድረስ በእስር ቤቱ ውስጥ ታጉረው ለተለያዩ በሽታዎችና ሞት አደጋ እየተጋለጡ መሆናቸው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የተባለው የዜና ወኪል ጥቅምት 3 2008 ዓ/ም ዘግበዋል።
         የኢህአደግ ስረአት ባለስልጣናት ሃገሪቱ አድጋለች፤ ሰላምና መልካም አስተዳደር ሰፍኖዋል በማለት በሚድያዎቻቸው እየገልፁ ባሉበት ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ ስደት እየፈለሱ ለሰቃይና ለሞት አደጋ እየተዳረጉ ያለ መሆኑን ደርጅቱ ጨምሮ  317 ሰደተኞች ከማላዊ አገር ወደ አገራቸው ለመመለስ 200 ሺ ዶላር እንዲሚያ ስፈልጋቸው ቢታወቅም ለነዚህ ኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚያሰብላቸው አካል ባለመኖሩ የተነሳ በአገረ ማላዊ የሚኖሩ የተለያዩ የገል ድርጅት ወኪሎች የሆኑትና ዲፕሎማት መሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት ለዜጎቹ የማያሰብ መሆኑን አመልክተዋል፣፣