Sunday, October 4, 2015

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አምባላጀ ወረዳ ለመጠጥ ውሃ ችግር ማቃለያ ተብሎ ከህዝብ የተዋጣው ገንዘብ በአስተዳዳሪዎች እየተጠፋፋ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።



የደቡብ ዞን አምባላጀ ወረዳ ነዋሪዎች በንፁህ የመጠጥ ውሃ እጥረት ምክንያት የግል ኑሮአቸውን ለመምራት ተቸግረው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው እነዚህ ዜጎች ለብዙ ሰዓታት እየተጓዙ የሚያገኙት ውሃም ንጽህናው ያልተጠበቀ በመሆኑ ለህመምና ለሞት እያጋለጣቸው እንደሚገኝ አስታውቋል።
ነዋሪዎቹ ያጋጠማቸውን የውሃ ችግር ለመፍታት ሲሉ ያዋጡት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ በወረዳዋ አስተዳዳሪዎች እንደተጠፋፋ የገለፀው መረጃው በተለይ የቤት ማራ ነዋሪዎች የተበላባቸውን ገንዘብ ለማስመለስ በተወካዮቻቸው በኩል ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረቡትን ጥያቄ “ እናንተ የተቃዋሚ ድርጂቶች ደጋፊዎች ናችሁ በማለት አስፈራርተው እንዳስመለሷቸው ለማወቅ ተችሏል።