Sunday, October 4, 2015

በትግራይ ክልል ድርቅ በአስከፊ ሁኔታ የሰውና የእንስሳት ህይወት እየቀጠፈ ሲሆን መንግስት ምንም እርዳታ አለማድረጉን አንዳንድ ምሁራን ለምንጮቻችን ገለፁ።



እንደምንጮቻችን ገለፃ ድርቁ በሰውና በእንስሳት ህይወት ላይ ከባድ ችግር እያደረሰ ሲሆን ዕርዳታ መስጠት አሁን ባይጀመርም  ለወደፊት በሚደረገው ዕርዳታ የመስጠት ዕቅድ ውስጥ የዓረና-መድረክ አባላት የሆኑ ነዋሪዎች “ዓረና ይርዳህ” በመባል ከዕርዳታው አሠጣጥ ዕቅድ ውጪ መደረጋቸውን ገልፆ ገዥው መንግስት ምንም የወሰደው የመፍትሄ አቅጣጫ ካለመኖሩ ባሻገር የህወሓት ካድሬዎች  ነዋሪ ገበሬዎችን “ከብቶቻችሁን ሸጣችሁ ተገላገሉ” በማለት መመሪያ እየሰጡ  መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ አብዛኛው ወረዳዎች በድርቅ አደጋ የተጠቁ ሲሆኑ እጅግ አስከፊ የሚባል ጉዳት ከደረሰባቸው ወረዳዎች መካከል አፅቢ ወንበርታ 12 ቀበሌዎች፣ የክልተ አውላዕሎ በርካታ ቀበሌዎች አብዛኛው የራያ ዓዘቦና ራያ አለማጣ ቀበሌዎች የኦፍላ ግማሽ ቀበሌዎች አብዛኛው የሕንጣሎ ወጀራት ቀበሊዎች ከግማሽ በላይ  የሰሓርቲ ሳምረ ቀበሌዎች አብዛኛው የጣንቋ አበርገለ ወረዳዎችና የምዕራባዊ ዞን በርካታ ቀበሌዎች  ተጠቃሾች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስካሁን ለእንስሳም ይሁን ለሰው እርዳታ ማቅረብ ያልተጀመረ ሲሆን በድርቅ የተጠቁ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑት የዓረና አባላት ከጥናቱ ውጭ እያደረጓቸው ይገኛሉ።