Monday, November 2, 2015

በትግራይ ክልል በደርቅ ምክንያንት ለተጎዱ ወገኖች እንዲውል ተብሎ እየገባ ያለው የእርዳታ ስንዴ የህወሃት አመራሮች ለግል ፋብሪካ እየሰጡ መሆኑን ታወቀ።



      መረጃው እንዳመለከተው የትግራይ ህዝብ አጋጥሞት ባለው የድርቅ መከሰት ምክንያት  የምግብ እጥረት  የህይወት አድን  ተብሎ  ከእርዳታ ሰጪ ደርጅቶች ወደ አገር እየገባ ያለ  የእርዳታ ስንዴ በርሃብ  ለተጠቁ ህብረተሰብ ሳይሰጡ የተወሰኑት የህወሃት ሃላፊዎች  ከግል ሃብታሞች  ጋር  በመሰማማትና በመሻረክ  50 ኪሎ ሰንዴ ዱቂት ከ250-300ብር  ለግል ፋብሪካ  እየሸጡና  በድርቅ አደጋ የተጎዱ ወገናች በረሃብ ህይወታቸው አደጋ ላይ እየወደቁ ባለበት ሁኔታ የረሃብ ተጎጂው ህብረተሰብ  በእጥፍ  እየጨመረ መምጣቱን መረጃው አክሎ አስታውቋል።
         በመቀጠልም ተሸጦ የሚገኘው የስንዴ ዱቄት ገንዘብ የሚበቃቸውን ያህል ለራሳቸው በመብላትና  በመስረቅ የተረፈውን ደግሞ ለአባይ ግደብ መስሪያ እየተባለ ህዝብ እየተራበና እየተሰቃየ ባለበት በአሁኑ ወቅት ገንዘቡን በመንጠቅ ህዝቡ አልፎለታል በሚል የተሳሳተ አባባል ለመሸፈን ቢሞክሩም።  በአሁን ወቅት  አጋጥሞ ያለውን የረሃብ አደጋ መልኩን  በማስቀየር የሙስና መረባቸውን ዝርግተው ለመዝረፍ እየተጠቀሙበት  ያለው አካሄድና ሰብአዊነት  አስተሳሰብ የሌለውና የጎደለው  መሆኑ ሊታወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮ እንዳመለከተው በዚህ ጉዳይ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በጥቅምት 8 /2008 ዓ/ም በለምለም ፋብሪካ ሁለት ትላልቅ ተሳቢ መኪናዎች ተጭነው  የመጣውን የእርዳታ ስንዴ  ዱቄት እንደሽጡት  ከቦታው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።