Friday, November 6, 2015

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲዊ ንቅናቂ (ትህዴን) ለረጅም ወራት በፓለቲካና በወታደራዊ ሲያሰለጥን የቆዩትን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች አሰመረቀ።




  የትህዴን ማሰልጠኛ ክፍል ሰልጣኝ አሰር የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው ለበርካታ ወራት በወታደራዊ  በፓለቲካዊ  በማሰልጠኛ የቆዩትን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኝ በጥቅምት 20 /02/2008 ዓ/ም የበላይ ሃላፊዎች፥ ወታደራዊ አዛዥ የትህዴን ደጋፊና ወንድማዊ ድርጅቶዎች እንዲሁም የትግል ደጋፊ በተገኙበት እንግዶዎች በደመቀ ሁኔታ አስመርቋዋል።
በዚህ ምረቃ ላይ የተገኙ የትህዴን የበላይ አመራር መኮንን ተስፋየ ባሰሙት  ቃል አንዳንድ ወላዋይ የሆኑ ታጋዮች የትግል መሰመር እየለቀቁ ቢሂዱም የትህዲን ድርጅት ትግል ግን  በተቃራኔው  በወታደራዊ በፓለቲካዊ  አቅም በመጠናከር ወደፊት በመገስገስ ላይ እንደሚገኝና  እንዲዚሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ አሰር ተመራቂዎች በቂ እውነተኛ ምስክር መሆናቸውን በንግግራቸው ባሰሙበት ወቅት ገልፀዋል።
   ይህን ብአል ለማድመቅ የሚያስፈልጉ ነገሮች አዘጋጅተው የተገኙ   የትህዴን የባህል ቡድን በተለያዩ የአገራችን ቋንቛዎች በተዋሃዱ ዜማዎችና ድርማዎች ይዘው የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎችም ዝግጅቶዎች ጨምረው ለተመራቂ ሰልጣኞዎች በደመቀ ሁኔታ አቅረበዋል፣ የተከበራችሁ ውድ ተከታታዮቻችን የአሰር ሰልጣኝ የምረቃ የብአሉን አከባበር ሙሉ ዝግጅት ከዜና በኃላ እንዲምናቀርብ እያሳውቅን መልካንም ቆይታ ይሁንላችሁ።