Friday, December 25, 2015

በአማራ ክልል የቅማንት ብሔረሰብ ከአማራ ብሄር መካከል በተነሳው ግጭት ከሁለቱም ወገኖች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖች ሙትና ቁስል እንደሆኑ ተገለፀ።



መረጃው እንዳመለከተው በአማራ ክልል ብሄረሰብ ቅማንት  ከአማራ  ብሄር መካከል  በተነሳው  ግጭት ከሁለቱም ወገኖች 300 ዜጎች ሙትና  ቁስል  እንዳሆኑና፣ በዚህ ሳብያም በነጋዴ ባህር፤ ሽንፋ፤ ሽህዲ፤ ኩኪትና  ቋራን ኣከባቢዎች  የሚኖሩ የብሄረ ሰብ  ቅማንት  በግጭቱ ምክንያት  ከሚኖርበት ቀየ  ተፈናቅለዉ ቤቶቻቸውና ንብረታቸው በሙሉ እንደወደመ ታወቀ።
     መረጃው  ኣስከትሎ ታህሳስ 9/ 2008 ዓ/ም ለሁለቱም ህዝቦች  የብአዴን  ከፍተኛ ባለ ስልጣኖች ሰብሰባ እንዳደርጉላቸውና  የስብሰባው መሪም ደመቀ መኮነን ስሆን  ካሳ ተክለብርሃንና አዲሱ ለገሰ ኣብረውት  የነበሩ  ሲሆኑ፣ ብሄረ ሰብ ቅማንት "እኛ ማንነታችን ይታወቅ  እኛው ራሳችን  በራሳችን መተዳደር ኣለብን፡ ብለን  ሃሳባችን ስለ ገለጽን ብቻ ብአዴን በላያችን ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ  አውርደዋል" ካሉ በዉሃላ  "የብሄረሰብ ቅማንት ጥያቄ መልሰነዋ የምትሉት ለብሄረሰብ ቅማንት የሚበታትን ነው" ሲሉ በምሬት ሓሳባቸ እንዳቀረቡ ለማወቅ ተቻለ።
    በአማራ ክልል ያጋጠመው ጥላቻ ኢህአዴግ ሊያረጋጋው ባለመቻሉ  ህዝቡ  በመከላከያ ሰራዊት እየተጠበቀ መሆኑንና ሃይለማርያም ደሳለኝ በበኩሉ በሚጋጩት ህዝቦች ላይ እርምጃ ዉሰዱ በማለት ወደ ወታደሮቹ ያወረደው ትክክለኛ ያልሆነ ትእዛዝ፣ ወተሃደሮቹ ግን ሰለማዊ በሆነ ህዝባችን ላይ    እርምጃ ኣንወሰድም ብለው በመቃወም ኣብዛኛዎቹ ወታደሮች ትጥቃቸው  በመጣል ላይ መሆናቸውንና እንዲሁም በዚህ ጉዳይ በተነሳ የሰራዊቱ ከፍተኛ ኣመራሮች ሰፊ ልዩነትና ያለመረዳዳት ተከስቶ እንዳለ የደረሰን መረጃ ኣስረድተዋል።