Tuesday, November 27, 2012

የ 31ኛ ክ/ጦር ክበብ ገንዘብ ያዥ ከ 200,000 ብር በላይ በመያዝ መጥፋቱን ቷውቋል ፣


በትግራይ ሰ/ምዕራብ ዞን የሚገኘው የ 31ኛ ክ/ጦር ክበብ ገንዘብ ያዥ የነበረው ወ/ር ዋክኔ ባሳዝን ከአከባቢው ሲሰወር ከ 200,000 ብር በላይ የክ/ጦሩ ክበብ ገንዘብ በእጁ እንደነበረ ለማወቅ ተችለዋል ፣   
በአሁኑ ግዜ በሰራዊቱ ውስጥ በተንሰራፋው ብልሹ አስሰራር ፤ የኢህአደግ መንግስት እያጋጠመው ያለውን ህዝባዊ ተቋውሞና ስርዓቱን በመጣል በሃገሪቱ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እየተካሄደ ያለውን የትጥቅ ትግል በመገንዘብ በርካታ የሰራዊቱ አባላት አምባገነኑን ስርዓት እየከዱ ሲጠፉ ማየት የተለመደ ሆኗል ፣
ባለፈው ሳምንት የዜና ዘገባችን በሰራዊቱ ውስጥ በሚታየው አድልዎ የተሞላበት አሰራር ምክንያት በርካታ የስርዓቱ ወታደሮች እርስበርሳቸው እንደሚገዳደሉና እራሳቸውንም የሚያጠፉ እንዳሉ መዘገባችን የሚታወስ ነው ፣