በደርሰን ዘገባ መሰረት በዓዲ-ጎሹ ፤ በሑመራና በሌሎች አከባቢዎች እየታየ ያለውን ህዝባዊ ተቋውሞ በሃይል
ለመጨፍለቅ ሲባል በርካታ አዳዲስ የደህንነት አባላትን ወደ አከባቢው በማሰማራት በሕብረተሰቡ ውስጥ እንዲበተኑ ተደርጓል ፣ እነዚህ
አዳዲስ የስለላ ወኪሎች የሚመሩት በካልአዩና በሪሁን በተባሉ የድህንነት ሃላፊዎች አማካይነት መሆኑን ቷውቋል ፣
በአከባቢው የተመደቡት እነዚህ የድህነነት አባላትና ካድሬዎች በህዝብ ላይ ኢሰብአዊ ተግባራት መፈጸም በመጀመራቸው
የአከባቢው ኗሪው ህዝብ ሁኔታውን በጥንቃቄ እየተከታተለው መሆኑ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል ፣