በደረሰን ዘገባ መሰረት በወረዳዋ ለብዙ ዓመታት በንግድ ስራ ተሰማርተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ነጋዴዎች
በአሁኑ ግዜ በመንግስት እንዲከፍሉ የተወሰነባቸውን ግብር በጥናት ያልተመሰረተና ግምታዊ ነው፣
ነጋዴዎቹ እንዲከፍሉ በመንግስት የተጠየቁትን ግብር ከሚያገኙት ገቢ የማይመጣጠን ብቻ ሳይሆን ነጋዴዎችን
ለኪሳራ ዳርጎ ከስራ ውጭ የሚያደርጋቸው በመሆኑ የተላለፈው ውሳኔው ዳግም ታይቶ መሻሻል እንዲደረግላቸው ለሚመለከተው አካል ጠይቀው
ነበር ፣ ነገር ግን የወረዳዋ መስተዳድር ሕዳር 8,2005 ዓ/ም ባካሄደው ስብሰባ ኗሪነቱ በከተማዋ የሆነ ማንኛውም ነጋዴ የተጠየቀውን የግብር መጠን መክፈል
ካልቻለ የንግድ ፈቃዱ ተቀምቶ ድርጅቱ እንዲዘጋ ባስተላለፈው ሃላፊነት የጎደለው ውሳኔ መሰረት ሶሞኑን ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ
መጀመሩን ቷውቋል ፣
በከተማዋ የንግድ ፈቃዳቸው ከታሸጉባቸው ነጋዴዎች መካከል ።-
1-አቶ አስማረ አረጋይ የህንጻ መሳሪያዎች መሸጫ ድርጅት ባለቤት
2-ወዲ-ሴሮ የህንጻ መሳሪያዎችን መሸጫና ማከፋፈያ
3-አቶ ጎይትኦም ማርቆስ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች መሸጫ ድርጅት
4-አቶ ሓድሽ ነጋሽ ‘የሰላም ሆቴል’ ባለቤት
5-አቶ አታኽልቲ ‘የወጋሕታ መጠጥና ምግብ ቤት’ ባለቤትና ሌሎች በርካቶች የሚገኙባቸው ሲሆን ባሁኑ ግዜ
ነጋዴዎቹ ድርጅቶቻቸው ከነንብረታቸው ስለታሸገባቸው ስራቸውን መስራት እንዳልቻሉ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል ፣