Friday, February 8, 2013

በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የሚገኙ የ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ወክለው በክልል ደረጃ በት/ቤቶች መካከል በሚደረገው የስፖርት ውድድር የሚሳተፉ ተማሪዎችን አመራረጥ ሂደት ስፖርታዊ ስነምግባርን የተከተለ እንዳልሆነ ቷውቋል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በአሁኑ ግዜ በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ባለው በትግራይ ክልል የሚገኙት ሁሉንም የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ያሳተፈ የስፖርት ውድድር ላይ ለመሳተፍ በሽረ እንዳስላሰ የሚገኙ ት/ቤቶችን ወክለው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችን በመምረጥ ሂደት በከተማዋ የ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ የተሰገሰጉ ካድሬዎች የተከተሉት አሰራር ህጋዊነትን የጎደለው ፤ ዓማውን የሳተና ስፖርታዊ ስነምግባር ከሚጠይቀው ውጭ ብቃቱ የሌላቸው ተማሪዎች በጥቅማ ጥቅም በውድድሩ እንዲሳተፉ የተደረገ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል፣
በሁኔታው ያልተደሰቱት ተማሪዎች ጥር 25,2005 ዓ/ም ምልመላውን ባካሄዱት ካድሬዎች ላይ ተቃውሞ በመቀስቀሳቸው ካድሬዎቹ ህይወታቸውን ለማዳን በአንድ ሻይ ቤት ውስጥ ገብተው መደበቃቸውን ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣