Friday, February 8, 2013

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ከ 20 ጥር 2005 ዓ/ም ጀምሮ በተማሪዎችና በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣








በደረሰን ዘገባ መሰረት በተማሪዎች የተቀሰቀሰውን በርካታ ጥያቄዎችን የያዘ ተቃውሞን ለማለዘብ ሲባል 25 ጥር 2005 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ተማሪዎችን በመሰብሰብ ጥያቂያችሁን የሚያቀርቡላችሁ 10 ተማሪዎችን ምረጡ በማለት ካስመረጡ ብሁዋላ ተመራጭ ተማሪዎችን በመካሄድ ላይ ላለው ተቃውሞ ዋና ቀስቃሽና ተጠያቂዎች ናቸው በማለት በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸውና እስካሁን ድረስም የት እንዳሉ የሚታወቅ ነገር የለም፣ በአሁኑ ጊዜ በሰላማዊ መንገድ የጀመረው ተቃውሞ ወደ ግጭት አምርቶ ፖለቲካዊ መልክ እየያዘ መምጣቱን ቷውቋል፣
በተማሪዎች የቀረቡ ጥያቄዎች
1-የምግብ አቅርቦት ይሻሻል
2-ትምህርት በአግባቡ ይሰጥ
3-በብሄሮች መካከል የሚደረግ ልዩነት ይቁም
4-በነጥብ አሰጣጥ ስርዓት አፈጻጸም ዙርያ የሚታየው ችግር ይስተካከል(በተለይ በሴቶች ላይ)
የመሳሰሉ ጥያቄዎችን በመያዝ ጥር 25,2005 ዓ/ም ቁጥራቸው 3000 የሚሆኑ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለውን ችግር ህዝብ እንዲያውቀው በሚል ከግቢው በመውጣት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሙ በማደረግ ላይ እያሉ ፌደራል ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ አስለቃሽ ጋዝ በመጠቀም ተማሪዎችን እንደበተናቸው ለማወቅ ተችለዋል፣
ተቃውመውን ተከትሎ ቁጥራቸው ያልታወቀ በርካታ ተማሪዎች በፖሊስ የተያዙ ሲሆን በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችን በተመለከተ የሚታወቅ ነገር የለም፣