Sunday, February 10, 2013

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጥር 25,2005 ዓ/ም በተማሪዎች በተካሄደው ተቃውሞ አንድ ተማሪ ከፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት መቁሰሉን ቷውቋል ፣



በጥር ወር መጀምርያ የተቀሰቀሰው የተማሪዎች ተቃውሞ እየተባባሰ መጥቶ ጥር 25,2005 ዓ/ም ስርዓቱ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በአጠቃላይ በህዝቡ እየፈጸመው ያለውን በደል መሸከም ያልቻሉ ተማሪዎች ተቃውማቸውን በአደባባይ ለመግለጽ ከዩኒቨርሲቲው ግቢ በመውጣት በተንቀሳቀሱበት ግዜ ፌደራል ፖሊስ በተማሪዎች ላይ ጥይት ተኩሶ በአንድ ተማሪ ላይ የመቁሰል አደጋ ማድረሱን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ፣
ይህ በእንዲህ እያለ 10 ከተለያዩ ብሄረሰቦች የመጡ ተማሪዎች የታሰሩ ሲሆን ሌሎች 10 የብሄረ ኦሮሞ ተወላጆች ደግሞ ከዩኒቨርሲቲው መባረራቸውን ለማወቅ ተችለዋል ፣