Sunday, February 10, 2013

‘ጀሃዳዊ ሃረካት’ በሚል ርእስ በኢህአዴግ ስርዓት ተቀነባብሮ በኢቲቪ የቀረበ ዶክሜንታሪ ፊልም የሞስሊሙ ማህበረሰብ ተቃውሞ ያጠናክረዋል እንጂ አይቀለብሰውም ሲሉ አንዳንድ ሙሁራን ገለጹ፣



የሃይማኖት ነጻነት ይከበር ፤ የህግ የበላይነት ይከበር ፤ መንግስት ከሃይማኖት እጁን ያንሳ በማለት በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ በሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለአንድ አመት የዘለቀና አሁንም በመደረግ ላይ ያለ ተቃውሞ መልኩን ለመቀየር በኢህአደግ ካድሬዎች የፈጠራ ድርሰት ተቀነባብሮ የተዘጋጀና ጥር 28,2005 ዓ/ም ምሽት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዲተላለፍ የተደረገ ዶክሜንታሪ ፊልም ስርዓቱ ከዚህ ቀደም እያደረገው ለመጣው ድራማ ቅጥያ ነው ሲሉ የተለያዩ ሙሁራንና ታዛቢዎች ገለጹ፣
አቶ ዑመር የተባሉ ወገን በሃሰት የተቀነባበረውን ድራማ የእስልምናንና የክርስትናን ሃይማኖት እምነት ተከታዮችን እርስ በራሳቸውን በማጋጨት የኢህአደግ ስርዓት ያጣውን ህዝባዊ ድጋፍ መልሶ ለማግኘት የሚያደረገው የተስፋ መቁረጥ ሙከራ መሆኑ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋና ጭምት በመሆኑ በመንግስት ፕሮፖጋንዳ ተታልሎ ለዘመናት በሁለቱ ሃይማኖት ተጠብቆ የቆየውን ወንድማማችነትንና መቻቻልን አፍርሶ ለግጭት አይነሳሳም በማለት አስተያየታቸውን አንጸባርቀዋል፣
የኢህአደግ ስርዓት በውሸት ፈጠራ በህዝብ መካከል ግጭት በመፍጠር ስልጣንን ማቆየት በሚል ፈሊጥ ከድሮ ጀምሮ ሲከተለው የነበረ የተለመደ ተግባር ቢሆንም አዝማሚያው ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ በመሄዱ ለበርካታ የህግ ባለሞያዎችና ባጠቃላይ ለመላው ህዝብ አነጋጋሪ ጉዳይ እየሆነ መምጥቷል ፣
የኢህአደግ ስርዓት በክርስትና እምነት ተከታዮችንም ሌላ ተመሳሳይ ድራማ ሊሰራ እንደሚችል አንዳንድ ወገኖች ይገልጻሉ፣