Sunday, February 10, 2013

በ 33ኛ ክ/ጦር የ 7ኛ ሬጅመንት 4ኛ ሻምበል ወታደሮች ግዳጃቸውን በካምፓቸው ግቢ ውስጥ ሆነው እንዲፈጽሙ እየተደረገ መሆኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በ108ኛ ኮር ፤ 33ኝ ክ/ጦር ፤ በ 7ኛ ሬጅመንት ፤ የ 4ኛ ሃይል አባላት ወታደሮች በመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደምብ መሰረት አንድ ወታደር በመከላከያ ለ 7 ዓመት አገልግሎት ከሰጠ ብሁዋላ ከሰራዊት የመሰናበት መብት አለው ይላል፣ ነገር ግን በተግባር ሲታይ ደምቡ ስራ ላይ ሲውል አይታይም በዚህም ምክንያት አገልግሎታቸውን ከአጠናቀቁ ብሁዋላ ከሰራዊት ለመሰናበት በተደጋጋሚ የጠየቁ የ4ኛ ሃይል አባልት እንደ ጥፋተኞች ተቆጥረው በካምፓቸው ውስጥ ብቻ ሆነው ግዳጃቸውን እንዲፈጽሙ እየተደረገ ነው ፣ ወታደረቹ ያሉበትን ህይወት የእስር ቤት ያክል እንደሆነባቸውና ከቃሊቲ እስር ቤት የሚለየው ነገር ቢኖር ትጥቅ በመያዛቸው ብቻ መሆኑን ይናገራሉ፣
ወታደሮቹ በተደጋጋሚ ስንብት ጠይቀው የተከለከሉ በመሆናቸው ምክንያት ጦሩን ይክዳሉ በሚል ስጋት ከካምፕ እንዳይወጡ ቢደረገም ባገኙት አጋጣሚ እግራቸው ወደመራቸው ከመሄድ ያገዳቸው ነገር የለም ፣
በተመሳሳይ በሰሜን አየር ምድብ የሚገኙ አባላት ከቦታቸው እንዳይንቀሳቀሱ ሲባል ስልጠና በሚል ሰበብ ወታደሮችን በአንድ ቦታ በማሰባሰብ በመላው የመከላከያ ሰራዊት አባላት እየተነሳ ያለውን የስንብት ጥያቄ እንደማይፈቀድ በይፋ መነገሩ ለማወቅ ተችለዋል ፣