በአዋሽ ወንዝ አከባቢ በእርሻ ሲተዳደሩ የነበሩ ኗሪዎች ለአመታት ሲጠቀሙበት የነበረ በወንዙ ዳር የሚገኝ
ለም የእርሻ መሬት ለኢንቨስተሮች እንዲሰጥ በመንግስት ስለተወሰነ የአከባቢው ኗሪዎች ቀያቸውን ለቀው ያለምንም ቅድመ ዝግጅት ገሌ
ወደ ተባለ ምንም ዓይነት መሰረተ ልማት ወዳልተሟላለት ቦታ እንዲሄዱ እየተደረገ መሆኑ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
በደረሰን ዘገባ መሰረት ከቀያቸው የተፈናቀሉትን የአዋሽ ወንዝ አከባቢ ኗሪዎችንና በአጠቃላይ የክልሉን ህዝብ
ለማሳመን ሲባል በፋር ህዝብ ዘንድ እንበ አባት የሚታዩትን ሃንፈሬ ዓሊሚራህን ከአመሪካ በማስመጣት አዋሽ ፤ አሳይታ ፤በራሕለይ
፤ ጭፍራንና አፊምቦን በሄሊኮፕተር ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ተደርጓል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በአዋሽ ወንዝ አከባቢ የኢህአደግ ስርዓት በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በመቃወም
ከፍተኛ ተቃውሞ በመቀስቀሱ ምክንያት በአከባቢው ውጥረት ነግሳል፣