Tuesday, February 5, 2013

በአማራ ክልል ፤ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፤ በፍኖተ ሰላም ወረዳ ፤ ከቀበሌ እስከ ወረዳ ለሚገኙ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ከመጠጥ ሱስ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ መተላለፉን ለማወቅ ተችለዋል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በፍኖተ ሰላም ወረዳ ከቀበሌ እስከ ወረዳ ድረስ ባለው መዋቅር ውስጥ ተመድበው በመንግስት ስራ ላይ የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች ከመጠጥና ሃሽሽ ሱስ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እንዲያመጡ መመሪያ ተላልፋል፣ ትእዛዙ የወረደው በወረዳዋ የጸጥታ ሃላፊ ሲሆን እንዲህ አይነቱ መመሪያ ለምን አስፈለገ የሚል ነገር እስካሁን ድረስ በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም ፣ የወረደው መመሪያ ያልተለመደ በመሆኑ በሁኔታው የተረበሹ የወረዳዋ ሰራተኞችና ሃላፊዎች መንፈሳቸውን ማረጋጋት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችለዋል፣
በወረደው አዲስ መመሪያ ግራ የተጋቡና መቀበል ያቃታቸው የወረዳና የጣብያ ሃላፊዎችም የኢህአደግ ባለስልጣናት በዘረፉት የህዝብ ሃብት በህግ ሊጠየቁ ይገባል ሲሉ መደመጣቸውን ከፍኖተ ሰላም ከተማ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣