ከሚያገኙት ገቢ ጋር ያልተገናዘበ ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ በኢፍትሃዊው የኢህአደግ መንግስት የተወሰነባቸው
በሸራሮ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች የተጠየቁትን ግብር መክፈል ስላልቻሉ የንግድ ድርጅቶቻቸው እንዲታሸጉ መደረጉ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
የንግድ ድርጅቶቻቸው ከታሸጉባቸው ነጋዴዎች መካከል።-
1-አቶ ዮዋሃንስ ዓንዳይ የአንድ ሉካንዳ
ቤት ባለንብረት ሲሆኑ የተጠየቁት ግብር 280 ሽ ብር
2-አቶ ሃይለ የሸቀጣ ሸቀጥ ባለንብረት ሲሆኑ የተጠየቁት ግብር 300 ሽ ብር
3-አቶ ሓድሽ ሙሉ የህንጻ መሳሪያዎች መሸጫ ድርጅት ባለንብረት ሲሆኑ የተጠየቁት ግብር 1.6 ሚልዮን
4-አቶ ሓጎስ አማረ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ባለንብረት ሲሆኑ የተጠየቁት ግብር 113 ሺ ብር
5-አቶ አታኽልቲ ባህልቢ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች መሸጫ ድርጅት ባለንብረት ሲሆኑ የተጠየቁት ግብር
180 ሺ ብር
6-መንግስቱ ይርጋለም በከተማዋ የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ወኪል አከፋፋይ ሲሆኑ የተጠየቁት ግብር 4.4 ሚልዮን
ብር
7-ጨበር በሚል የሚታወቅ ነባር ታጋይ የሸቀጣ የሸቀጥ ሱቅ ባለንብረት ሲሆን የተጠየቀው ብር 260 ሽ ብር
8-አቶ ሃይሉ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ባለንብረት ሲሆኑ የተጠየቁት የግብር መጠን 300 ሽ ብር ይገኙባቸዋል
፣
በአሁኑ ግዜ ነጋዴዎቹ መንግስት የጫነባቸውን ከፍተኛ የግብር መጠን ለመክፈል አቅሙ ስላላገኙና የንግድ ድርጅቶቻቸውም
ስለታሸጉባቸው ስራ ፈትተው በችግር ላይ ይገኛሉ፣
ካሁን ቀደም ባቀረብነው የዜና ዘገባ በሃገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎቹ መንግስት በጣለባቸው ከፍተኛ ግብር ምክንያት
ድርጅቶቻቸው ታሽገው ከስራ ውጭ ሆኖው በችግር ላይ የወደቁ በንግድ ስራ ሲተዳደሩ የነበሩ ዜጎችን አስመልክተን መዘገባችን የሚታወስ
ነው ፣