Sunday, February 23, 2014

በመቀሌ ዞን መስተዳድር ዓዲ ሓውሲ በተባለው ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የዓዲ ሃቂ ነዋሪ ህዝብ ለረጅም ግዜ አጋጥሞት ያለውን ንፁህ የመጠጥ ውሃ እጥረት መፍትሄ ሊያገኝለት እንዳልቻለ ተገለፀ።



በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ህብረተሰብ በንፁህ ውሃ እጥረት ለዓመታት እየተሰቃየ መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ በተለይ በዓዲ ሃውሲ ከባብያዊ መስተዳድር የክፍለ ከተማ ዓዲ ሓቂ ነዋሪዎች በንፁህ ውሃ እጥረት ምክንያት ማህበራዊ ኑሮውን ለማከናወን ተቸግሮ እንዳለ የተገኘው መረጃ አስታወቀ።
     ነዋሪዎቹ ለዚሁ መፍትሄ ላልተገኘለት ንፁህ የመጠጥ ውሃ ኣጥረት ምክንያት በማድረግ በየካቲት 4/2006 ዓ/ም የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ በሞኮሩበት ግዜ የስርአቱ አስተዳዳሪዎች የተቃውሞ ሰልፉን አስተባብረዋል ላሉዋቸው 16 ሰዎች ፀረ ልማት ሃይሎች ናቸው በማለት በአካባቢው በሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አማካኝነት ዓዲ ሃውሲ አካባቢ ወደ ሚገኘው እስር ቤት ወስደው እንዳጎርዋቸው ለማወቅ ተችለዋል።
      የዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ኣስተዳዳሪ በሆነው አታኽልቲ በርሀ የተባለው ግለ ሰብ ትእዛዝ ከታሰሩት ዜጎች ውስጥ አቶ ሓድጉ አማረና አቶ ወርቁ በርሀ ከዓዲ ሓቂ፤ ኣቶ ካህሳይ በርሄና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው ከከተማው በተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።