Thursday, March 27, 2014

በአድዋና አካባቢዋ በየካቲት 10 /2006 ዓ.ም በትህዴ የተበተነው ፋምብሌት በስርዓቱ ባለ-ስልጣናት ላይ ስጋት ስለፈጠረባቸው ንፁሃን ዜጎችን በማሰር ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ማዕከላዊ ዞን አድዋ ከተማ ውስጥ በድርጅታችን የተበተነው ፋምብሌት በርካታ ስለትህዴን መረጃ ያልነበራቸው ወጣቶችና የአገር ሽማግሌዎች የተበተነውን ወረቀት በማንበብ እንደዚህ አይነት ስራ የሚሰራ ድርጅት በትግራይ ውስጥ አለ ወይ በማለት በግልፅ በመናገራቸው ብቻ በከተማዋ ዋና አስተዳዳሪ ትእዛዝ እንዲታሰሩ እንደተደረገ ለማውቅ ተችልዋል።
    የከተማዋ አስተዳደር በወጣቶች ላይ እየወሰደ ያለው የማሰር እርማጃ በአድዋ ነዋሪ ህዝብ ላይ ትልቅ ስሜት ፈጥሮ ስለቆየ በቅርቡ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለምን ልጆቻችን ታሰሩ የሚል ካባድ ጥያቄ በመነሳቱ በስብሰባው ላይ የተገኘው የከተማዋ ዋና አስተዳዳሪ ልዑል አበራ የትህዴን ፋምብሌት በየካቲት 11 ዋዜማ በመበተኑ ምክንያት ትልቅ ሥጋት ስለፈጠረብን ነው ከዚህ ፋምብሌት ጋር ትስስር ያለው ንግግር ለተናገረ ሰው ልናስርው የቻልነው ብሎ እንደመለሰ ታውቋል።
   በመጨረሻ ይህ ባልስልጣን እኛ ማነኛውም ወጣት እንደነዚህ አይነት የተበተኑ ፅሁፎችን አንብቦ ያልሆነ መስመር እንዳይዝና ከትህዴን ጎን እንዳይሰለፍ በመስጋት የወሰድነው እርምጃ ነው ሲል ላደረገው ንግግር በስብሰባው ተካፋይ የነበርው ህዝብ በበኩሉ እኛ እናተ ያላችሁንን ብቻ ሳይሆን ተግባር ላይ የምናውል የፈለግነው አንብበን ስለ ሃገራችን አንዳንድ መረጃዎችን ማወቅ መብታችን መሆኑን መገንዘብ አለባችሁ አንብበን ደግሞ ምን እንደምናደርግ ለኛ ይመለከተናል እንዳልዋቸውና ልጆቻችንን በእንደዚህ አይነት ጥርጣሬ ማሰራችሁ ግን ፍፁም ፀረ ህዝብ የሆነ አካሄድ እየተከተላችሁ ነው እንዳልዋቸው መረጃው አክሎ አስገንዝብዋል።