በአማራ ክልል ሰሜን
ጎንደር ዞን የተሻለ የቀን ስራ ይገኝበታል ወደተባለ አካባቢ አባጢርና መተማ ከተለየዩ የሃገራችን ክፍሎች የሚሄዱ ዜጎች በአካባቢው
ባሉ አስተዳዳሪዎቻና የፀጥታ ሃላፊዎች ፀጉረ ‘ለወጥ ናችሁ እየተባሉ ከአካባቢው በፍጥነት እንዲወጡ በመደርግ ላይ እንድሚገኙ ከአካባቢው
የደረሰን መረጃ አመለከተ።
በመረጃው መሰረት የአካባቢው አስተዳድሪና የፀጥታ ሃላፊዎች ስራ ፈልገው
ለሚሄዱ ወገኖች እናንተ በዚህ አካባቢ መስራት የምትችሉት መጀመርያ 600 ብር ከፍላችሁ መታውቂያ ወረቀት ከአስተዳደሩ ማምጣት አለባችሁ በተባሉበት ግዜ እነዚህ ወገኖች በበኩላቸው
ጉልበታችንንና ላባችንን እያፈሰስነ ያለነው ለናንተ ለመስጠት ሳይሆን ሰርተን እንድንጠቀም ነው ብለው እንደመልሱላቸው ለማወቅ ተችልዋል።
ባጋጠማቸው ተቃዉሞ የተበሳጩ የስርዓቱ ባለስልጣናት ተላላኪ ካድሬዎቻቸውን
በማሰማራት ሰላማዊ ሰዎቹን ከተሰማሩበት አካባቢ እያደኑ በመሰብሰብ ላይ እንዳሉና በተለይ ደግሞ 600 ብር አንከፍልም ብለው ከተቃወሙት
ውስጥ የናእዴር አዴት ተወላጅ የሆነው ሃብቶም በርሀ ለተባለ ዜጋ አንተ በኮንትሮባንድ ስትነግድና ትክክለኛ ያልሆነ መታወቅያ ስትሸጥ
ተይዘሃል በሚል መሰረት የሌለው ምክንያት የፌደራል ፖሊስ በየካቲት 18/2006 ዓ.ም ለሊት ገድለውት እንዳድሩ ከቦታው የተገኘው
መረጃ አመለከተ።