Saturday, March 29, 2014

በሽሬ ከተማ ውስጥ የካቲት 11 የህወሓት ምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተካሄደው መድረክ እንዳልተሳካ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለጹ።



በዞኑ አስተዳደር እንደአንድ ትልቅ እቅድ ተይዞ'' የህወሓት ህልውና ለማረጋገጥ ሁላችን እንነሳ"በሚል በተዘጋጀው የገንዘብ መሰባሰብያ መድረክ ጥሪ የተደረገላቸው ባለ ሃብቶች፤ መምህራንና ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች  ለተደረገላቸው ጥሪ ስለልተቀበሉት በቦታው እንዳልተገኙና በቦታው የተገኙት የተወሰኑ ባለ ሃብቶችም ቢሆኑ ያዋጡት የገንዘብ መጠን በጣም አነስተኛ እንደነበር በመድረኩ የተገኙ ምንጮቻችን አስረዱ።
   መረጃው በማስከተል በ01፤ 03 ፤04’ና ፤05  ቀቤሌዎች ውስጥ ለሚገኙ ባለሃብቶች በተደረገላቸው ጥሪ የተገኙት የተወሰኑት በመሆናቸው ብመድረኩ የተሰበሰበ ገንዘብ አንስተኛ በመሆኑ ምክንያት የስርአቱ ካድሬዎች በተደረገላቸው ጥሪ ያልተገኙ ሰዎች እነማን እንደሆኑ እያጠኑዋቸው እንደሆነ ታውቋል፣
   ይህ በየካቲት 11 ስም የተካሄደው የገንዘብ መሳባሰብያ መድረክ" ባለፈው  ጥር 28/ 2006 ዓ/ም የህወሓት ህልውና ለመረጋገጥ ሁላችን እንነሳ" የሚለውን የወያኔ መሪ መፈክር መሰረት ያደረገ እንደሆነ  ለማወቅ ተችሏል።