Saturday, March 29, 2014

በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ የቴሌፎንና ኔት-ዎርክ አገልግሎት ጨርሶ በመቋረጡ ምክያት ህዝቡ ለከፍተኛ ሽግር ተጋልጦ እንዳለ ምንጮቻችን ከቦታው ገለጹ።



   በወረዳው በሚገኙ ኣልፋ-ቁጭ፤ ዛልማና ስንቶም በሚባሉ ቀበሌዎች የመብራት፤ የቴሌፎንና የኔትዎርክ አገልግሎት ካለፈው የካቲት 6/ 2006 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠት በማቛረጡ ምክንያት፤ ነዋሪዎች ስራቸው ማካሄድ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋልጦው እንደሚገኙ። ከበታው የደረሰን መረጃ አስረድተዋል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዊ ዞን ስኮላ ወረዳ የሚገኙ የ01 አምቢሲና የጉንድል ቀበሌዎች ከባለፈው የካቲት 4/ 2006 ዓ/ም ጀምሮው እስካሁን የመብራትና የቴሌፎን አገልግሎት ማግኘት ባለመቻላቸው ሕብረተ-ሰቡ በችግር ላይ መውደቁ ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው በመጨረሻ በአካባቢው በንግድና ሌሎች የኢቨስትመንት ስራዎች የተሰማሩ ባለሃብቶች አጋጥሞ ባለው የኤሌክትሪክና የቴሌፎን አገልግሎት መቛረጥ ምክንያት ብሶታቸው በማሰማት ላይ መሆናቸው የተገኘው መረጃ አክሎ አስታውቀዋል።