ነዋሪዎቹ በተከሰተው
የውሃ እጥረት የተነሳ ለመጠጥና እለታዊ ምግባቸው ለመዘጋጀት እንደተቸገሩ የጠቆመው መረጃው እንደ አማራጭ ፅዳቱ ካልጠበቀ ውሃ መጠቀም
ግድ ስለ ሆነባቸው በውሃ ወለድ በሽታወች ለከፋ ችግርና ስቃይ እንደተጋለጡና ይህንን ፅዳቱ ያልተጠበቀ ውሃም በቀላሉ ማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት በተለይ አቅም የሌላቸው ቤተሰቦች ለሌላ የባሰ ችግር
ተጋልጠው እደሚገኙ መረጃው አስታውቀዋል።
በከተማዋ ውስጥ ለተከሰተው የውሃ እጥረት ሃላፍነት ወስዶ መፈትሔ የሚሰጥ
አካል ባለመኖሩ የተቆጡ ነዋሪዎች በአካባቢው ወደ ሚገኙ የዞኑ የውሃ ልማት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ያኔ ኣጉምዝ በወኪሎቻቸው አድርገው
ላቀረቡት ጥያቄ ከአቅሜ በላይ ነው የሚል መልስ ስለሰጣቸው እስካሁን ድረስ መፍትሄ የሚሰጣቸው አካል እንዳላገኙለማወቅ ተችሏል።