Monday, March 31, 2014

በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች ለጣና በለስ መስኖና ለስዃር ፋብሪካ ግንባታ ተብሎ የተወሰደው መሬት ተለዋጭ ቦታ ስላልተሰጣቸው ነዋሪዎቹ ችግር ላይ መውደቃቸው ተገለፀ።



ነዋሪዎቹ ከረጅም አመታት በፊት ሲጠቀሙበት የቆዩ የእርሻ መሬታቸው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ካሳና ተለዋጭ መሬት ሳይሰጣቸው ከሁለት አመት በፊት በድንገት በመንግስት መሬታቸው በመነጠቁ ምክንያት በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ወገኖቻችን ችግር ላይ እንደወደቁ ለማወቅ ተችለዋል።
     ይህን ከ75 ሺ ሄክታር በላይ የሆነው ከህዝብ የተነጠቀው መሬት ተለዋጭ መሬት እንዲሰጣቸው ለዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ባዘዘው ጫኔ በተደጋጋሚ ባቀረቡት ጥያቄ ውጤት ማግኘት ስይችሉ ቀርተው በድጋሚ ተስፋ ሳይቆርጡ 6 ወኪሎቻቸው በመምረጥ ወደ ፌደራል ስኳር ልማት ኮርፐሬሽን ሃላፊ በመሄድ ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡም አሁንም መጀመርያውኑ ከተሰጣቸው መልስ የተለየ ባለመሆኑ ምክንያት ችግራቸው ሰሚ ጀሮ አጥቶ ብሶታቸውን በተደጋጋሚ በማሰማት ላይ እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።