Monday, March 31, 2014

በአማራ ክልል አዊ ዞን ዚገም ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ለመስረተ ልማት እንዲዉል ተብሎ ከህዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንድሚገኙ ተገለፀ።



ከወረዳዋ ነዋሪዎች ለመሰረት ልማት እንዲውል ተብሎ 900ሺ ብር የሚደርስ የተዋጣው ገንዘብ ለታሰበለት አላማ ሳይውል የወረዳዋ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ተካፍለው ስለ-በሉት ከዕለት ጉርሻው ተቆርጦ የተወሰደበት ህብረተሰብ ይህንን ድርጊት በሰማበት ግዜ በነዚህ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ላነሳው ተደጋጋሚ ጥያቄ ሰሚ አካል እንዳላገኙ ለማወቅ ተችልዋል።
      ከ900 ሺ ብር በላይ የተዋጣው የህዝብ ገንዝብ በገጠር ላለው የመብራት ችግር ለማቃለል በሶላር የሚሰራ መብራት ለመትከል ተብሎ አቶ አዲሱ ብርሃኑ በተባለ ባለስልጣን እንደተሰበሰበ የገለፀው ይህው መረጃ አዲሱ ግን የገባውን ቃል ወደጎን በመተው የህዝቡን ገንዘብ ከወረዳዋ አስተዳዳሪዎቻና ካድሬዎች ጋር ሁኖ ለግል ጥቅሙ እንዳዋለው ታውቋል።
    ገንዘባቸው የተበላባቸው የወረዳዋ ነዋሪዎች መፍትሄ ለማግኘት ብለው ወደ ወረዳዋ የፖሊስ አዛዥ ኤንስፔክተር አስፋው አጥናፉና በአካባቢው ወደሚገኝ ፍርድ ቤት በመሄድ ላቀረቡት አቤቱታ መልስ እንዳላገኙና በአንፃሩ አቤቱታ ሰሚ የተባሉ አካላት በገንዘቡ መጥፋት ንክኪ ስለ ስላላቸው ለዚህ አስነዋሪ ወንጀል ሸፋፍነው ማለፍ እንደመረጡ የአካካባቢው ምንጮች በላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችልዋል።