Friday, April 11, 2014

ለአባይ ግድብ መስሪያ ተብሎ ይጓጓዝ የነበረ ሲሚንቶና የተለያዩ ንብረቶች በጎንደር ከተማ ለግል ነጋዴዎች እየተሸጠ መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



ይህ ደርባን ከተባለ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለአባይ ግድብ መስሪያ ተብሎ በትላልቅ መኪኖች ይጓጓዝ የነበረ ሲሚንቶ  ኮድ 3 የሴሌዳ ቁጥሩ 019256 አዲስ አበባ የሆነው የጭነት መኪና ለአባይ ግድብ መስሪያ ተብሎ ያጓጉዘው ለነበረው ሲሚንቶ ጎንደር ከተማ ሲደርስ መጋቢት 22/2006 ዓ/ም ሌሊት ለግል ነጋዴዎች እንደተሽጠ ከገዙት ነጋዴዎች መካከልም ሃለቃ ክፍላይ አለም የተባለ የጎንደር ከተማ ነዋሪ እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።
      እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ህዝብ ከልጆቹ አፍ እየተቦጨቀ ለአባይ ግድብ መስሪያ እየተባለ ለሚሰበሰበው ገንዘብ ቁጥጥር የሚያደርግለት አካል ስለሌለ ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት የሃብት ምንጭ መሆኑ ያሳዘናቸው የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ምሬታቸውን እየገለፁ መሆናቸው መረጃው አክሎ አስረድተዋል።