Friday, April 11, 2014

በወልቃይት በሚገኘው ስኳር ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ቦንድ አልገዛችሁምና የድርጅት አባል አልሆናችሁም በሚሉ ሰንካላ ምክንያቶች በስርዓቱ ካድሬዎች እየተቸገሩ መሆናቸው ከቦታው ያገኘነው መረጃ አስታወቀ።



እነዚህ በምዕራብ ትግራይ ዞን ወልቃይት ወረዳ እየተሰራ ባለው ስኳር ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች የገዥው ፓርቲ አባል እንዲሆኑና ለአባይ ግድብ መስሪያ የሚሆን ገንዘብ ቦንድ እንዲገዙ እነደታዘዙ ይህን ማድረግ ካልቻሉ ግን ከስራ የሚባረሩ መሆናቸውን የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ካድሬዎች ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው የጠቀሰው መረጃው ሰራተኞቹ ግን ለአባይ መስሪያ ገንዘብ እንከፍላለን አባል እንድንሆን ግን አታስገድዱን ሲሉ ተቃውሞ ማሰማታቸው ተገለፀ።
      ይህ በእንዲህ እንዳለ የድርጅት አባል አንሆንም ለአባይ ግን እንክፍላለን ካሉት 15 ሰራተኞች መካከል፥ ሃብቶም ወዲራያ የተባለው የፕሮጀክቱ ሂሳብ ሹም አሰፋ ብርሃኔና ሌሎች ስማቸው ያልተገለፁ ሲሆኑ በአሰሙት ተቃውሞ ምክንያትም ለ5 ቀን ከስራቸው እንደታገዱ ለማወቅ ተችሏል።