Saturday, May 31, 2014

በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በተከሰተው የስንብት ጥያቄን አስመልክቶ በመከላከያ ሚኒስተር አቶ ሲራጅ ፈጌሳና ጀነራል ሳሞራ የኑስ መሪነት የዕዝና የክፍለጦር አዛዦች ያካሄዱት ስብሰባ ያለምንም ፍሬ እንደተበተነ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



ይህ ከግንቦት 10 እስከ 15 2006ዓ/ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት በመከላከያ ሚኒስተር አቶ ሲራጅ ፈጌሳና ጀነራል ሳሞራ የኑስ የተመራ በመኮንኖች ክበበ ሲካሄድ የሰነበተው ስብሰባ የዕዝና የክፍለጦር አዛዦች ስንብትን አስመልክቶ የቀረበውን ሃሳብ ቢቀበሉትም በመከላከያ ሚኒስተር አዛዦች ግን ከአንድ ክፍለጦር 630 ወታደሮች ማሰናበት አይቻልም የሚል መምሪያ እንዳወረዱና ስብሰባውም ያለ-ስምምነት እንደተበተነ የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የ7ና የ10 አመት አገልግሎታቸውን የጨረሱ የሰራዊቱ አባላት እንዲሰናበቱ የወጣው ደንብ ከእያንዳንዱ ሬጅመንት ከ60 እስከ 80 የሚሆኑ ወታደሮች እንዲሰናበቱ ተብለው ለብቻቸው ተለይተው ከቆዩ በኋላ በክፍለጦር አዛዦችና በመከላከያ ሚኒስተር ባለስልጣናት መካከል በተፈጠረው ያለመስማማት ምክንያት የስንብቱ ደንብ ተግባራዊ ሊሆን እንዳልቻለ መረጃው አክሎ አስታውቋል።