እነኚህ በፀለምቲ ወረዳ ቀበሌ ዲማ-ምንጫራ እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው አርሶ-አድሮች ባለፈው መጋቢት ወር
2006 ዓ/ም በስርአቱ ካድሬዎች ማዳበርያ እንዲወስዱ ግፊት ቢደረግላቸውም የማዳበሬያው ዋጋ ከልክ በላይ ጭማሪ ስለተደረገበት ከአቅማቸን
በላይ ነው በማለታቸው ብቻ የ6 ወር እስር እንደተፈረደባቸው ለማወቅ ተችለዋል፣፣
ወንጀል ሳይኖራቸው እንዲታሰሩ ከተፈረደባቸው መካከልም አቶ ሃፍቱ አለባቸው፤
ቄስ አለበል ኪዳነና ከሰቆጣ-ስላሴ ቀበሌም አቶ አስረስ ንጋቱ የተባሉ እንደሚገኙባቸው መረጃው አስታውቀዋል፣፣
ማዳበሪያ አልወሰዳቹሁም በሚል ምክንያት አርሶ-አደሮችን እንዲታሰሩ ማድረግ
በፀለምቲ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሃገራችን አከባቢዎችም እየተፈፀመ መሆኑን ይታወቃል፣፣