Sunday, July 13, 2014

በጎንደር ከተማ ሌብነት በከፍተኛ ሁኔታ በመስፋፋቱ ምክንያት በአንድ ሳምንት ብቻ ከ50 በላይ የተለያዩ ሱቆችና መጋዘኖች እንደተሰረቁ ምንጮቻችን ከከተማዋ አስታወቁ፣፣



    በጎንደር ከተማ ስርቆት ከግዜ ወደ ግዜ በከፍተኛ ሁኔታ ለመስፋፋቱ ዋናው ምክንያት  በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ከሌቦች ጋር እጅና ጓንት በመሆን እየሰሩ በመሆናቸው ሌቦቹ የሚቆጣጠራቻው አጥተው ለነዋሪው ህዝብ እያስቸገሩት እንዳሉ ምንጮቻችን ለከተማዋ ነዋሪዎች መስረት በማድረግ። ከላኩትን መረጃ ለማወቅ ተችለዋል፣፣
   ከተዘረፉት ነጋዴዎች መካከልም አቶ ማሓመድ መስዑድ፤ አቶ ዋኘው ከበደ፤ ሃለቃ አለምና ሌሎች በርከት ያሉ ባለስቆች የዚህ ሰለባ እንደሆኑ መረጃው ጨምሮ አስረድተዋል፣፣