Thursday, July 17, 2014

በናእዴር ዓዴት ወረዳ ውስጥ ለሚገኝ ህብረተሰብ ለአንድ ኩንታል ማዳበርያ በ1,300 ብር እንዲገዛ በመገደድ ላይ እንዳለና ይህንን ተግባራዊ ለማያደርግ እርዳታ አይሰጥህም እየተባለ የማስፈራርያ ቃል እየዘነበበት እንደሚገኝ ታወቀ።



በመረጃው መሰረት በናእዴር ዓዴት ወረዳ የአበባ ዮውሃንስ ቀበሌ ነዋሪ ህዝብ ለአንድ ኩንታል ማዳበርያ በ1300 ብር ለመግዛት እቅም የለኝም ብሎ ለተናገረም እርዳታና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች አይሰጥህም እየተባለ የቀበሌው አስተዳዳሪዎች በሆኑት ተክለ ሃጎስና የስራ ባለደርቦቹ የማስፈራራት ዛቻ እየደረሰባቸው እንዳለ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
     መረጃው በማስከተል ለወረዳው ተብሎ የሚመጣውን የእርዳታ እህል በተቸገሩ ወገኖች እጅ ሳይደርስ በአስተዳዳሪዎች እንደሚጠፋፋና ወገናዊነት በተጠናወተው መንገድ ለዘመዶቻቸው እየታደለ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
     በቅርብ ቀን በወረዳዋ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገብረስላሴ ገብሩና በፀጥታ ክፍል ሃላፊው ደስታ ገብረሃወርያት በተመራው ስብሰባ ላይ የተገኘው ህዝብ አቶ ገብረስላሴ ገብሩ ለህዝቡ ተብሎ የመጣውን የእርዳታ እህል ለግል ጥቅሙ ስለሚያውለውና በጉቦ የተጨማለቀ ስለሆነ እኛን አያስተዳድረንም ከስልጣኑ ይውረድልን የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን ወደ ዞን እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችለዋል።
     በመጨረሻም በህዝቡ አያስተዳድረንም ተብሎ የተገለጸውን የቀበሌው አስተዳዳሪ ፈፅሞታል የተባለውን ችግር ከበላይ ሃላፊዎቹ ጋር ተመካክሮ ያደረገው በመሆኑ አሁንም በተሰጠው ስልጣን ላይ ሆኖ እየቀጠለ መሆኑን የተመለከተው የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ብሶቱን እየገለፀ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃው  ያመለክታል።