በቅርብ ቀን በሲራጅ ፈጌሳና ጀነራል ሳሞራ የኑስ መሪነት በአዲስ አበባ የተካሄደው የጀኔራሎች ስብሰባ ዋናው
አጀንዳው የተቀነሱትን የሰራዊት አባላት ማሰናበትና እነሱን የሚተኩ አዲስ ሰልጣኞች ለማስገባት ተብሎ በመንግስት እየተካሄደ ያለው
የምልመላ ስርአት መሆኑና የቀረበውን ሃሳብ በተሰብሳቢዎቹ አካላት ተቀባይነት እንደሌለው ከተገለፀ በኋላ ስብሰባ ግርግር በተሞላበት
መንገድ መፈፀሙ ታወቀ።
በስብሰባው ውስጥ የተገኙት ጀነራሎች
በተለያዩ ወረዳዎች ወጣቶችን በማስገደድ ወደ ውትድርና እንዲገቡ እየተደረገ ያለውን አሰራር ህጋዊነት የለውም፤
በገንዘብና በሌሎች ጥቅማጥቅሞች በማታለል ወደ ውትድርና የማስገባት ሂደት መቅረት አለበት በማለት የጀነራል ሳሞራ ዮኑስን ሃሳብ
ስለተቃወሙት ጀነራል ሳሞራ ዮኑስ ስብሰባውን ለመምራት በመቸገሩ ምክንያት ያለፈ ታሪክ እያመጣ ሊያስፈራራቸው እንደሞከረ ለማወቅ ተችለዋል።
ቀደም ሲል ሳሞራ ዮኑስ በሚመራው ስብሰባ ላይ ከሱ ጋር ሆነው የሚመሩ ኮሚቴ
ተቋቁመው ቢቆይም ኮሚቴዎቹ በሃሳብና በእጅ ብልጫ በውሳኔ ላይ ስላሸነፉት ኮሚቴውን በማፍረስ ከመከላከያ ሚኒስተር ሲራጅ ፈጌሳ ጋር
በመሆን ስብሰባውን ለመምራት በሞከረበት ሰአት በተሰብሳቢዎቹ ሳሞራ አምባገነን ነህ፤ ክስልጣንህ ተነስ ምርኩስ እስክትይዝ ድረስ
አትጠብቅ ብለው መናገራቸውን የደረሰን መረጃ አመለከተ።
በመጨረሻም በተከሰተው ሁኔታ የተናደደው ሳሞራ የኑስ መድረኩን እያስፈራራ በመራበት ግዜ በመድረኩ መሪዎችና
በተሰብሳቢዎች መካከል በተፈጠርው ያለመረዳዳትም ከአፋር ክልል ወጣቶችን እያስገደደ ወደ መከላከያ ሰራዊት ሲልክ የነበረው ፍስሃ
ኪዳነ (ፍስሃ ማንጁስ) የተባለው ጀነራል የሚገኝባቸው ስብሰባውን ረግጠውት መውጣታቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።