Friday, July 11, 2014

የኢህአዴግ ስርአት የወረዳ አስተዳዳሪዎች እያንዳዳቸው 20 ሰው ወደ ውትድርና እንዲመለምሉ በተሰጣቸው መመርያ መሰረት፣ ወጣቱን በማስገደድ እያስታጠቍቸው መሆናቸውን ከተለያዩ ወረዳዎች የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



እነዚህ ከበላይ አለቆቻቸው መመርያ የተሰጡት የወረዳ ሃላፊዎች፣ ወጣቱ ወደ ውትህድርና እንዲገባ ፍላጎት ስለሌለው መመርያውን መተግበር አይቻልም የሚል ሃሳብ ቢያቀርቡም፣ የስርአቱ የበላይ ባለስልጣኖች ግን ሃገርና መንግስት እንዲጠበቅ ከፈለጋችሁ ህዝቡን አሳምናችሁም ይሁን አስገድዳችሁ የተሰጣችሁን ኮታ ሟሟላት የናንተን ብቃት ይጠይቃል ብለው እንደመለሱሏቸው ለማወቅ ተችለዋል።
    ይህን አይነት ሃላፊነት የሌለው መመርያ እየሰጡ ካሉት ውስጥ በአፋር ክልል የፀጥታ ሃላፊ የሆነው ስዩም አወልና ከመከላከያ ተወክሎ የመጣው ሜ/ ጀነራልን ፍስሃ ኪዳነ (ፍስሃ ማንጁስ ) ጋር በመሆን፣ በዚህ ሳምንት ውስጥ ለበራህሌ ነዋሪ ህዝብ በመሰብሰብ ወጣቱ ወደ ሰራዊት እንዲገባ ቅስቀሳ ባደረጉበት ሰአት ተቀባይነት ስላላገኙ ስብሰባው ላይ ለተገኙት 9 ወጣቶች ብቻ አስገድደው ወደ መቐለ በመውሰድ፣ ለያንዳዳቸው 1500 ብር አበል በመስጠትና በገንዘብ በመደለል ወደ ውትድርና በራሳቸው ፍላጎት እንደመጡ በማስመሰል ወደ ማሰባሰብያው ማእከል እንዳስረከብዋቸው ቢታወቅም፣ ተገደው ከተወሰዱት 9 ሰዎች 7 ጠፍተው ወደ ትውልድ አገራቸው መመለሳቸውና የተቀሩት 2 ሰዎችም መቐለ ከተማ ውስጥ እንደተሰወሩ ለማወቅ ተችለዋል።
   በተመሳሳይ መንገድ በአማራ ክልል ሰኔ 27/ 2006 ዓ/ም ከ 8 እስከ 10 ክፍል የደረሱትን ከእድሜ በታች የሆኑ ወጣቶች በማስገደድና በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች አታልለው ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ውትድርና ለመውሰድ በሞኮሩበት ግዜ፣ የተማሪዎቹ ወላጆችና ያካባቢው ህዝብ ለአቅመ አዳም ያልደረሱትን ህፃናት ወደ ውትድርና የመውሰድ ተግባር ይቁም በማለት፣ በመንግስት ላይ ብሶታቸውን እየገለፁና አቤቱታቸውን እያቀረቡ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከጎንደር ከተማ መግለፃቸው መረጃው አክሎ እስረድተዋል።